የኦንላይን ድር ድጋፍ

    ለተጨማሪ ድጋፍ ፣ ዝመናዎች ፣ ፊርምዌር ፣ ዳውንሎዶች እና አጋዥ ስልጠናዎች ይህንን ይጎብኙ፥www.sony-mea.com/en/electronics/support

    የእውቂያ ማዕከል

    ባለሙያዎቻችን ፈጣን መፍትሄዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ እዚህ ይገኛሉ።

    የቴክኒክ ድጋፍ እና ጥገናዎች

    ከዚህ በታች ባለው የአገልግሎት ማእከል ማንኛውንም ቴክኒካዊ ችግር የሚፈቱላቸው የእኛን መሐንዲሶችን ያግኙ


    የ Sony ምርት ስለገዙ እናመሰግናለን።

    እባክዎ የዋስትና ደምቦችን እና ሁኔታዎችን በተመለከተ ከዚህ በታች ይመልከቱ

    Sony የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ FZE (“እኛ”, “Sony”) ለ Sony ምርቶች በክፍል (1) እስከ (4) እንደተመለከተው የአምራች የዋስትና ሽፋን ያቀርብልዎታል  (“የአምራች ዋስትና”)። 

    እባክዎ ከዚህ በታች የቀረበውን የዋስትና ማረጋገጫ ደምቦች እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ያንብቡ እና ይረዱ።

    የአምራች የዋስትና ማረጋገጫ ደምቦች እና ሁኔታዎች፥

    1) በአምራች የዋስትና ማረጋገጫ ስር ሽፋን ያላቸው የ Sony ምርቶች፥

    የ Sony ምርት ከዚህ በታች እንደተዘረዘረው የ Sony ብራንድ ምርቶች ማለት ሲሆኑ፣ እርስዎ እንደ ደንበኛ የገዟቸው፣ ይህም የግዢውን ቀን ፣ የምርቱን የሞዴል ስም ፣ የቸርቻሪው ስም/ማህተም የሚያመለክት፣ ትክክለኛ የሆነ የግዥ ማረጋገጫ (የመጀመሪያ የክፍያ መጠየቂያ ወይም የሽያጭ ደረሰኝ) ያላቸው ማለት ነው።

    በዋስትና ሽፋን ያላቸው የ Sony ምርቶችየዋስትና ጊዜ
    ቴሌቪዥኖች1 ዓመት
    DVD እና BD ማጫወቻ1 ዓመት
    የቤት ትያትር1 ዓመት
    HiFi ኦዲዮ ሲስተም1 ዓመት
    HiFi ክፍለ አካል1 ዓመት
    ሬዲዮ ካሴት1 ዓመት
    ሬዲዮ1 ዓመት
    ዲጂታል የሙዚቃ ማጫወቻ1 ዓመት
    IC ድምጽ መቅጃ1 ዓመት
    የጨዋታ መቆጣጠሪያ3 ዓመታት**
    የጨዋታ ማዳመጫዎች1 ዓመት
    ፕሮ ኦዲዮ1 ዓመት
    ገመድ ኣልባ ስፒከር1 ዓመት
    ሄድፎን (የብሉቱዝ ሞዴሎች ብቻ)1 ዓመት
    የመኪና ድምጽ - ES Series ዋና ክፍል፣ ንዑስ ድምጽ ማጉያዎች እና ድምጽ ማጉያዎች*3 ዓመታት
    የሚለዋወጥ ሌንስ ካሜራ1 ዓመት
    የሚለዋወጥ ሌንስ1 ዓመት
    ካምኮርደር እና የኣክሽን ካሜራ1 ዓመት
    የፈጠራ ፕሮ ካሜራ እና ሲኒማ መስመር (እባክዎ ከታች ያለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ)1 ዓመት

     

     ሞዴሎች

     

     

     

     

     

     

     

     

     

    የፈጠራ ፕሮ ካሜራ

    ILX-LR1
    BURANO
    HXR-NX100
    HXR-NX200
    HXR-NX800
    ILME-FR7
    ILME-FX3
    ILME-FX30
    ILME-FX30B
    ILME-FX6
    ILME-FX6T
    ILME-FX6V
    PXW-Z190
    PXW-Z190T
    PXW-Z190V
    PXW-Z200
    PXW-Z90T
    PXW-Z90V

     

     

    ሲኒማ መስመር

    PXW-FX9T
    PXW-FX9TK
    VENICE (MPC-3610)
    MPC-3626 (VENICE 2 : 6K)
    MPC-3628 (VENICE 2 : 8K)

    *የ ES Series ንዑስ-woofers እና ድምጽ ማጉያዎች በዋስትና አይሸፈኑም።
    ** እስከ ኤፕሪል 30 ድረስ ለሚደረጉ ማናቸውም ግዢዎች የ1 ዓመት ዋስትና ዋስትና 2025

    ከላይ በተዘረዘረው ውስጥ የሌሉት ምርቶች፣ በአምራች ዋስትና ሽፋን ያልተሰጣቸው ናቸው እና የዋስትና መረጃውን ለማግኘት እባክዎ የአከባቢዎን ቸርቻሪ ያነጋግሩ።

    2) በአምራች የዋስትና ማረጋገጫ ስር ሽፋን የሌላቸው ዕቃዎች፥

    (i) መለዋወጫዎች (እንደ ሪሞት ፣ አዳፕተሮች ፣ ኬብሎች እና ተመሳሳይ ዕቃዎች ያሉ)

    (ii) አላቂ እቃዎች (እንደ ባትሪ እና ተመሳሳይ ዕቃዎች ባሉ በምርት ዕድሜ ውስጥ በየጊዜው መተካት ይፈልጋሉ ተብለው የሚታሰቡ ክፍሎች)

    (iii) የምርቱ መዋቢያ አካላት (እንደ ካቢኔቶች ፣ ቁልፎች ፣ ማብሪያ ማጥፊያዎች እና ተመሳሳይ ዕቃዎች ያሉ)

    (iv) ሶፍትዌር እና ማንኛውም ማዘመኛዎች

    3) የአምራች የዋስትና ሁኔታዎች፥

    ሀ) ከአምራች ዋስትና ተጠቃሚ ለመሆን፣ የ Sony ምርትን የገዙበትን ቀን የሚያሳይ የተፈቀደለት የሻጩን የክፍያ መጠየቂያ ወረቀት/ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርብዎታል።

    ለ) የቀረበው የአምራች ዋስትና፣ የተጠቀሰውን የ Sony ምርት ለመጠገን ብቻ ነው እንጂ፣ የምርቱን ምትክ ለማቅረብ ኣይደለም፣ ወዘተ።

    ሐ) የቀረበው የአምራች ዋስትና ለሚከተሉት ሽፋን አይሰጥም፥

    - ከ እና ወደ አገልግሎት ማእከል መጓጓዝ ፣  የመርከብ ወጪ ፣ የአገር ውስጥ ግብር እና ሌሎች ሊከሰቱ የሚችሉ ከትራፊክ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ወጪዎች።

    - የአንድን እቃ የማስወገድ እና የመጫን/የመትከል።

    - ማንኛውም የምርቱ አካላዊ ጉዳት ወይም ከልክ በላይ ሙቀት በመኖሩ ምክንያት የተቃጠለ አካላት፣ በእርጥበት ፣ ፈሳሽ ፣ ነፍሳት ፣ የውጭ ነዳጆች ፣ምክንያት መበስበስ/መዛግ ፣ የውስጥ የመስታወት መሰበር ፣ አደጋዎች ፣ የመጓጓዣ ጉዳት ፣ የኃይል መለዋወጥ ፣ የምርት አላግባብ መጠቀም ፣ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ማጽዳት ፣ ማርጀት እና መቀደድ ፣ የተፈጥሮ አደጋ ፣ የፈጣሪ ስራ ፣ እና ወይም የአጠቃቀም መመሪያዎችን የሚጥስ ወይም በእነዚህ መመሪያዎች ውስጥ ያልተካተተ ማንኛውም ክዋኔ።

    - በ Sony ፈቃድ ባልተሰጠው ማንኛውም ሰው የተነካኩ ወይም ጥገና የተደረገላቸው የ Sony ምርቶች።

    - የ Sony ምርቶች ፣ የሞዴል ስማቸው ወይም መለያ ቁጥራቸው ከተጠቀሰው ጥቅል ፣ የክፍያ መጠየቂያ / ደረሰኝ ፣ ወይም በምርቱ ካርቶን ላይ ካለው ፣ ጋር የማይዛመድ፣ ወይም ከተቀየሩ/ከተለወጡ ፣ ከተወገዱ ወይም ሆን ተብሎ ጉዳት ከደረሰባቸው።

    መ) የአምራቹ የዋስትና ማረጋገጫ ከላይ በተጠቀሱት ሁኔታዎች ስር ተፈፃሚነት ዮረዋል ወይም አይኖረውም ብለው ሊፈርዱ የሚችሉት፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በ Sony ፈቃድ የተሰጣቸው የአገልግሎት ማዕከላት ብቻ ናቸው።

    4) ማስተባበያ፥

    በሚመለከታቸው ህጎች እስከሚፈቅደው ድረስ፣ በ Sony ምርቶች ላይ ተፈፃሚነት ያለው ዋስትና አይኖርም (የጥራት አጥጋቢነት ወይም ለተወሰነ ዓላማ ብቁነትን ጨምሮ)። በአምራቹ የዋስትና ማረጋገጫ በተገለፁ መንገዶች ብቻ፣ መብትዎን ማስከበር ወይም በእርስዎ ላይ የደረሰውን ማንኛውንም ጉዳት ማዳን ይችላሉ። Sony፣ በውል ፣ በማጭበርበር ፣ ወይም በሌላ መልኩ በመመርኮዝ ከ Sony ምርቶች ወይም ከነዚህ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ፣ የውሂብ መጥፋት ወይም በድንገት ፣ በተዘዋዋሪ ፣ በልዩ ሁኔታ ወይም ተያያዥ በሆኑ ጉዳቶች ምክንያት (ጥቅማጥቅሞችን ወይም ትርፎችን ማጣትንም ጨምሮ) ተጠያቂ አይሆንም።

    የአምራች ዋስትና ለመጠቀም እባክዎ የሚከተለውን ፈቃድ ያለው የ Sony የአገልግሎት ማእከል ያነጋግሩ፥

    ግሎርየስ ኅላ.የተ.የግል ኩባ.

    ማህተማ ጋንዲ መንገድ 1 ወለል ሳሙኤል ደረሳ ህንጻ ፒያሳ ከላየን ፋርማሲ ኣጠገብ አዲስ አባባ። ኢትዮጵያ

    ስልክ፥

    +251 111570013

    +251 111570261

    ኢሜይል፥ service@glorious-plc.com

    የአገልግሎት ሰዓታት፥

    ከሰኞ-ሓሙስ; 08:00am - 12:30pm / 02:00pm - 05:30pm

    ዓርብ; 08:00am - 11:30am / 02:00pm - 05:30pm

    ቅዳሜ; 08:00am - 12:30 pm